Mission Statement

Mission Statement

የአገልግሎታችን ትኩረት በጸጋው ወንጌል ላይ የተመሠረተ አገልግሎት መስጠት

• የመጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃልነት ያለውንም ስልጣንና የእምነት ምንጭነቱን ማስተማር።
• ጌታችን እኛን ከሕግ እርግማን የዋጀበት ፥ ከአባቱ ጋር ያስታረቀበት ፥ ከዘላለም ሞት ወደ ዘላለም ሕይወት ያሸጋገረበት የመስቀሉ ስራ ቀዳሚነትና ዋነኛነት በሚጠበቅበት አገልግሎት ማገልገል።
• ወርዱና ስፋቱ የማይታወቀውን የሰማዩን አባት ፍቅር ፥ ከመጠን ያለፈውን የጌታ ጸጋ ፥ አማኞች እንዲታነጹበት እያስተማርን በፍቅርና ጸጋ የዳበረ ሕይወት እንዲኖራቸው እንገለግላለን።
• ጌታችን የዘላለም ሊቀ ካህን ሆኖ በአብ ቀኝ የተቀመጠበትን ሰማያዊ አገልግሎቱን የቅዱሳን መመኪያ እንዲሆን እናስተምራለን።
• በእምነት መጽደቅን ፣ ዳግም ውልደትን ፣ የወንጌልን የንስሐ መልእክትና በመንፈስ ቅዱስ የመታተምን ምስጢር እናስተምራለን።
• ክርስቶስ እየሱስ ራስ ወደ ሆነባት ቤተ ክርስቲያን ብልቶች ልንሆን የተጨመርንበትን የክርስቶስን አካል ምስጢር እናስተምራለን።
• ከትክክለኛው ወንጌል ጋር ከማይጣጣሙ የስሕተት ትምሕርቶች አማኞች በቃሉ ሐይልና ጸጋ እንዲጠበቁ እናገግላለን።

የዳኑትን በጌታቃልና ጸጋ ማሳደግ

• የአማኞች የግል ሕይወት ከቤተ ክርስቲያን የአካል ሕይወት ጋር እየተቀናጀ፣ ጌታ በሚሰጣቸው ጸጋ እንዲያድጉ እናገለግላለን።
• ለአካል እድገት እንቅፋት የሆነውን በማስወገድ ለትንሣኤ ሕይወት ምክንያት የሆነውን የመስቀል ማእከላዊነት አማኞች እንዲያተርፉበት እናስተምራለን።
• አማኞች ኢየሱስ ክርስቶስን ብቃታቸው በማድረግ መንፈሳውያን ሆነው እንዲኖሩ፣ ከእርሱ የተነሳ የሚገኘውን የድል ሕይወት እናስተምራለን።
• አማኞች ለመንፈስ ቅዱስ አመራር ራሱንም በመግለጥ ሊሰራ ለሚወደው የጸጋ ሥራ ሁሉ የተመቸ አቋምና እምነት እንዲኖራቸው እናገለግላለን።
• እያንዳንዱ አማኝ በመንፈስ እየተሞላ ፣ የመንፈስ ፍሬ እያፈራ ፣ በመንፈስ ቅዱስ የጸጋ ስጦታዎች እየታገዘ የሚያገለግልበት እድል እንዳይጓደል እናስተምራለን።
• ምዕመናን ማሕበራዊ ኑሮአቸው ከመንፈሳዊ ሕይወታቸው ሳይለያይ በትዳራቸው ፣ በሥራ ገበታቸው ለጌታ ክብር መኖር እንዳለባቸው እናሳስባለን።
• አማኞች በማራናታ መንፈስ ተሞልተው የጌታን ዳግመኛ ምጽዓት በናፍቆት እንዲጠብቁ እያስተማርን የመጻተኛ ኑሮአቸውን እንዲያስቡ እናስምተራለን።

የቤተ ክርቲያንን አንድነትና እድገት መጠበቅ

•ቤተ ክርስቲያን የመንፈስ አንድነቷን ለመጠበቅ የጠብ መግደያ የሆነውን መስቀል ያማከለ የወንጌልን እውነት በማስተማር ከዘረኝነትና ከወገናዊነት እንድትጠበቅ እናስተምራለን።
• ቤተ ክርስቲያን ወደ ክርስቶስ ሙላት እንድትደርስ ጌታ በሰጠን ጸጋ እናገለግላለን።
• ቤተ ክርስቲያን በመካከልዋ ጌታ ያስቀመጠው መቅረዝ በሐጢያትና በአለመታዘዝ እንዳይወሰድባት ንስሐንና ቅድስናን በማስተማር ንጽሕናዋን በበጉ ደምና በመንፈስ ቅዱስ ሐይል እንድትጠብቅ እናስተምራለን።
• ቤተ ክርስቲያን ከዋጃት ጌታ ጋር የምትሆንበትን የመነጠቋንና ለበጉ ሰርግ መዘጋጀትዋን ችላ ሳትል እንድትኖር የጌታን መምጣት በሚያቻኩል የናፍቆት መንፈስ እንድትኖር እናስተምራለን።
• ቤተ ክርስቲያንን እንደ ጌታ ሃሳብ ለመንግሥታት ፤ በሥልጣን ላይ ለተቀመጡና ለሰዎች ሁሉ የምሥጋና ፤ የምልጃና የልመና ጸሎት በማድረግ እንድታገለግል ማነሳሳት።
• የወንጌልንሥራመስራት ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን ታምና በምትኖረው ኑሮ ለጌታዋ ክብር ለዓለም ብርሃንና ለምድር ጨው እንድትሆን ማስተማር።
• የታላቁን ተልእኮ አገልግሎት ለመፈጸም ወንጌልን ላልዳኑት በመመስከር ፤ ያመኑትን በሳል የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በማድረግ፣ ለአገልግሎትም የሚበቁበትን ስልጠና በመስጠትና በማሰማራት ማገልገል።
• ለታመሙት መፈወሻ እንዲሆን ጌታችን በስጋው የተቀበለውን መከራ በመታመን ሕመምተኞች እንዲፈወሱ በጸሎት እናገለግላለን።
ከመንፈሳዊ አገልግሎት ርቀው ለሚገኙ ምቹ የሆነ ፕሮግራም በአቅራቢያቸው በመጀመር አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት በየስፋራው እንዲጀምሩ ማበረታታትና መደገፍ።
• በሬዲዮን ኢንተርኔትንና የተለያዩ የኮሙኒኬሽን መንገዶች በመጠቀም መንፈሳዊ ትምሕርቶችን መስጠት።
• መንፈሳዊ ትምሕርቶችን በመጻሕፍት፣ በትራክቶችና በመጽሔቶች በማዘጋጀት ማገልገል።
• የወንጌልን እውነት ሳናመቻምች ትክክለኛ መንፈሳዊ አቋም ካላቸው ጋር የወንጌል ማሕበረተኛ በመሆን በጋራ ሊሰራ በሚችል የጌታ ሥራ እንተባበራለን።
• በጌታ መከራ የሚቀበሉትንና ድሖችን በረድኤት አገልግሎት በመርዳት ማገልገል ድኆችንና ስለ ጌታ መከራ የሚቀበሉትን በረድኤት አገልግሎት በመደገፍ በጌታ ርህራሄና ፍቅር ያለንን በማካፈል እናገለግላለን።
• በሐገራችንም ሆነ በሌሎች ስፍራዎች በሚደረጉ እውነተኛና ትክክለኛ ከሆኑ የረድኤት ሥራዎች ጋር በመሆን እንሳተፋለን።